Skip to content

በግፍ የዜጎችን ሕይወት ማጥፋቱ በአስቸኳይ ይቁም

EPRP pressrelease Amh August 2018-1

እንጻፍ ካልንማ–5

If we have to write it – 5

የህብረት ጥያቄ አሁንም በአግባቡ አልተያዘም

on hibret

የህብረት ጥያቄ አሁንም በአግባቡ አልተያዘም

(Read/Print in pdf)

ከፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሬዲዮ

ፖለቲካና ሀገር አድን ትግል ማንም በዘፈቀደ ቀዶ ሊጠግነው የሚነሳበት ሊሆን አይገባም። ከጥቂት ሳይሆን ብዙ ዓመታት ወዲህ ያለው አስተያየትና እምነት ግን ይህ አይደለም። ሁሉም ገብቶ የሚንቦጫረቅበት ያልተጣራና ያልታጠረ ኩሬ ሆኖ ይገኛል። የማያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል ነውናም ገና ከአያያዙ ይፈለጋል የሚባለው ህብረት የሚሆን አለመሆኑ ግልጽ ሆኖ ያታያል። ህብረት ህብረት የሚለው ጩኸትም አንዳንዴም በወያኔ ጉረሮ የሚጮህ ይሆንና ውድቅ ሆኖ ይቀራል።

በቅድሚያ እስካዛሬ የተደረጉትን የህብረት ጥረቶች ጥንካሬና ድክመት ወይም ለምንስ እንዳከተሙ ጠንቅቆ መመርመር አስፈላጊ ይሆናል። ጥረቶቹን በጀምላ ማውገዙ ትክክል ካለመሆኑ ሌላ ትምህርት የሚስጥም አይደለም። ለችግሮችም አንድ ወይ ሁለት ድርጅትን ሁሌም መወንጀሉ ተገቢ ካለመሆኑ ሌላ ሲመረመር መሰረትም የለው። ኢዴሓቅ እንዳይመሰረት ዕንቅፋት የሆነው የአንድ ድርጅት መሪ ለምሳሌ ግንባሩ ተቋቁሞ ሚናውም ሲያከትም ሁለት የግራ ድርጅቶች አፈረሱት ብሎ ሲከስ ተድምጧል። ሌሎች ደግሞ ይህንን ግንባር ሆነ ማዕከል ሆኖ የመሰረተውን ህብረት አንድ ራሱን–አንድ ድምጹን ይዞ– አፈረሰው ብለው ሲከሱም ተደምጠዋል። ኢሕአፓ ከዚህ ሁሉ በኋላ የወሰደው አቅዋም ተመክሮውን መሰረት ያደረገ ከመሆኑ ሌላ ለከሳሾቹ መድረኩን የሚለቅላችው ነበር። ሆኖም ሲተባባሩና ፍሬ ያለው ስራ ሊሰሩ ሲችሉ አልታዩም። ወደ ኋላ መለስ ብለን ፍሬ የሰጡ ጥረቶች ቢሆኑም ድክመታቸው ለምንድን ነበር ብንል የሚከተሉትን መገንዘብ እንችላለን፤

  1. መለስተኛ አስማሚ መሆን ባለበት መርህ ግብር ላይ በቂ ስምምነት አልነበረም። ባለመሆኑም ለምሳሌ ግንጠላን የሚያቀነቅኑ ግንባሮች ጋር የተደረገው ሙከራ ገና ሲጀምር በአፍጢሙ እየተደፋ አስቸግሯል።
  2. በኢትዮጵያ አንድነት አመንን የሚሉትም ቢሆኑ ሁሉም በሀገሪቷ ሉዓላዊነት የሚያምኑ ሳይሆኑ አንዳንዶቹ ለባዕዳን በማደራቸው ከሌሎቹ ጋር ልዩነቱ ሳይውል ሳያድር አፍጦ እየመጣ ለችግሩ በር ከፍቶ ጥረቶቹን ጎድቷል።
  3. በህብረቱ በእኩል ድምጽ ደረጃ የሚሰለፉት ውስጥ ቁጥራቸው ትንሽ ያልሆኑት የአባላቸው ቁጥር ጥቂት፣ አቅማቸው ገለባና ህልውናቸውም አጠያያቂ የሆኑ እንደነበሩ በኢዴሀቅም ሆነ በህብረቱ ሙከራ ወቅት የታየ ነው። ጠንካራና አሰባሳቢ ማዕከል ለህብረቶቹ አለመኖሩ ወይም እንዳይኖር መደረጉም ትልቅ ጉዳት አድርሷል።  በምሳሌነት ይጠቀስ የነበረው በአል ፋታህ ማዕከልነት የተሰባሰበው የፓለስታይን ነጻ አውጪ ግንባር (ፒ ኤል ኦ) ተገቢ ቦታ ተሰጥቶት ቢሆን ምናልባትም ከስህተትና ድክመት ያድን ነበር የሚለው አሁንም አነጋጋሪ ሊሆን የሚገባው ነው። ከዚሁ ተያይዞ ሙሉ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ደግሞ የህብረት ጥረቶችን ገና ከጅማሮአቸው ወያኔ እንደ ጨጎጊት ተጣብቃባቸው እንደምትገኝ ነው። በቅርቡ ደግሞ ማየየት የተገደድነው ሀፍረት፣ አፍራሾችና ከፋፋይ ግለሰቦችና ቡድኖች የህብረት ጠሪና ፈላጊ ነን ብለው ሲራወጡ ነው።

ካለፉት ተመክሮዎች ትምህርትን ማግኘት በተመለከተ ብዙ ተብሏል ተጽፏልና ይህን ሚዛን ሰጥቶ መገመገም በቅድሚያ አስፈላጊ ነው። ይህ ሳይደረግ አሁንም የምናየው ግን ያለፈው ስህተት ሲደገምና ሊደረግ የሚገባው ጥረት ሲደናቀፍ ነው። ይህ ደግሞ ለወያኔ እንጂ ለትግል እንደማይጠቅም ግልጽ ሆኖ አለሁ ይለናል። አሁንም ግንጠላን ከቶም ካልተዉና ካልተሻሻሉ ቡድኖች ጋር ህብረት ይፈለጋል። ከንቱ ልፋት። አሁንም ህልው ያልሆኑ ሀይሎች ህብረት ፈጠርን ማለት ብቻ ሳይሆን ደፍረውም፣ ይሉኝታንም አፈር አብልተው፣ ማዕከል ሆነን እናሰባስባችሁ ብለው ጥሪ ሲያሰሙ ይደመጣል። ከ24 ዓመት የወያኔ ባለጌና ዘረኛ አገዛዝ በኋላም–በግንቦት 20 የደነቆረ እንበልና–ከወያኔ ጋር እንሰባሰብ ብለው ሳያፍሩና የፖለቲካ መሃይምነታቸውን ሳይደብቁ ጥሪ የሚያሰሙም አሉ። የጨረባ ተዝካር ! ማን ሞኝ ነውስ ከወያኔ ጋር፤ ከወያኔ ቅጥረኛና ግንባር አፍራሾች ጋር፤ ከድርጅት ከፋፋዮች ጋር እንደገና ተታሎ ህብረት በሚል ከንቱ ጥረት ጊዜ ሊያጠፋ የሚስማማው? መልሱ እንዳልነው በፖለቲካው መስክ ተመክሮ ያጣውና አሊያም የተጃጃለው ነው። መከራም ሊመክረው ያልቻለ ማለት ነው። አሁንም እንዳለፈው የቆሙት ለሀገር መሰረታዊ ብሔራዊ ጥቅም ሳይሆን ለባዕድ ያደሩ ጋር ለማበርና በዚያው ለመውደም ጥረቶች ይታያሉ። ጉድ የሚያሰኝ ነው። አውቆ ራስን ማጥፋት!

የሚሰራና ውጤት የሚኖረው ግንባር ለማቆም በቅድሚያ ድርጅቶች በኢትዮጵያ አንድነትና በዴሞክራሲ አጠቃላይ መርህ ላይ ተገቢው ስምምነት ሊኖራቸው ይገባል። ግንባር ለግንጠላ ሊሆን አይችልም። አንድነትና ግንጠላ የሚሉ ሊሰምሩና ሊታገሉ አይችሉም፣ አንዱ ወይ ሌላው አቅዋሙን ካልቀየረ ማለት ነው። ሀገር አድን ትግላችን ደግሞ ራሱን ሊሸራረፍና ለገንጣዮች መሳሪያ ሊሆን መታሰብም የለበትም። በመሰረታዊ አቅዋም ላይ ስምምነት ካለ ዝርዝር የመርሀ ግብር ነጥቦችን፣ ሕዝብ ሀገሩን ሲረከብ የሚውስንባቸው ይሆናል። ይህ ቢባል የአንድ ፓርቲ አምባገንነትን ማቀንቀንና እኩልነትና መብትን ለማፈን ማቀድ የሚደገፍ ሊሆን ይችላል ማለትም አይደል። ያለፈው ህብረት የሁለት ዓመት የውይይት ጥረት ቢሆንም መፍረሱ አልቀረም። ለምን ብለን መጠየቅ መመርመር ሲያንሰን ነው? ያም ሆኖ ግን አሁንም ቢሆን የእነቶሎ ቶሎ ቤት እንዳይሆን መጠንቀቁ አስፈላጊ ይሆናል። ማንም ቡድን አለሁ የማለትና እታገላላሁ የማለት መብቱን ማንም ሊነፍገው ባይገባም አምስት ቡድኖች ራሳቸውን ድርጅት ብለው ህብረት መስርተው ያላቸው የአባል ቁጥርና አቅም ግን የወያኔን ክብሪት ቡድን እንኳን የማይቋቋም ከሆነ ህብረት ከነዚህ በነዚህ ዋጋ ቢስ ነው። ለዚህም ነው ህልውና ያላቸው ማለትም ድርጅት የሆኑ፤ አባላት ያሏቸው፤ የሚንቀሳቀሱ፤ አቅምም ያላቸው፤ ወያኔም በዚሁ የተነሳ የሚፈራቸው ቢሆኑ ይመረጣል የሚባለው። ይህ የድርጅት ትምክሀት ሳይሆን ሀቅን መቀበልን የሚያመለክት ነው። ስለዚህም ህብረት ስንል ወያኔን በተጨባጭ ሊታገል የሚችል ህብረት ማለታችን እንጂ ለጥቅምና ንግድ ከትግል መስክ ርቆ ወይም አቅም አጥቶ አለሁ የሚለውን አይደለም ondeond።

ግንባር ምስረታ የቁም ነገር አያያዝን ይጠይቃል። በህብረተሰቡና በድርጅቶች የማይታመኑ ወይም ከባድ ተቃውሞ ያለባቸው የጥረቱ ማዕከል ሊሆኑ አይገባም። ሳይጀመር ያበላሹታል ወይም ሌላው ይሸሻል። ኢሕአፓ ለምሳሌ የቀረበበትን ክስ ባይቀበልም እስቲ ራሳችሁ በራሳችሁ ሞክሩና ህብረት ፍጠሩ ብሎ በራሱ ትግሉን ቀጠለ እንጂ ማዕከል ልሁን ብሎ አልደረቀም። ዛሬም የተቀየረ አቅዋም የለውም። ከገለባና ኢምንት–ያውም የስደት– ቡድኖች ጋር፤ ከአፍራሾችና አንጃዎች ጋር ባሉበት እስካሉም መቸም ቢሆን ህብረት በሚል መድረክ አልገናኝም ሲልም ከወዲሁ አቅዋሙን ግልጽ አድርጎ በማይፈይድ ጥረት ወይም እሰጥ አገባ ላለመግባት ነው። ከተመክሮ መማር ይሏል ይህ ነው። ዳግም ከረግረጉ አለመግባት፤ክጭቃው አለመዘፈቅ። ከዚህ ባሻገር ሁሉም ህብረት ህብረት ባይ ህብረትን በዕርግጥ ይፈልጋል ማለት አይደለም። ቢሆን ኖሮማ ተሰባሰብን እናንተም ኑ ተሰባሰቡ ባዮችና ግንባርና ጦር ነገ የሚሉን ሁሉ ስንት ተዓምር ባሳዩን ነበር። አልሆነም ግን። የዚህንም ምክንያት ማወቅ ከባድ አይደለም። የግንባር/ህብረት ምስረታውን ጥረት አቅምና ተዓማኒነት ያላቸው፤ ሊያስተባብሩም የሚችሉና ተመክሮም ያላቸው ቢሆን የተሻለ ይሆናል ማለት የግድ ነው። ይህንን ሀቅ መቀበልም ጥረቱን ወደፊት የሚወስድ ይሆናል። አለበለዚያ ጥረቶች ከንቱ ውይይቶችም ከጉንጭ አልፋነት የማያልፉ ሆነው ይቀራሉ። ይህን ሁሉ በመገንዘብ ኢሕአፓ የግንባርን ጥያቄ በተመለከተ ተገቢውን ምላሽ ሰጥቷል። ከጥቅም አልባ ስብስብ ነን ባይ ጥረቶችም ራሱን አርቆና ህልውናውን ጠብቆ፤ ጉልበቱና ገንዘቡን እንዳለፈው ሳያባክን እየታገለም ነው።

ለአውስትራሊአ ብሮድካስቲንግ አገልግሎት

iewo aesed media2 (4)

ሴቶች የነፃነት መብታቸውን ሳይጎናፀፉ ማህበራዊ እድገት ሊኖር አይችልም!

Meglecha March 8 2015 INT. W. Day.1

Image

በየነ ዛሬም (Beyene Today)

beyene

ኢትዮጵያዊነት የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መሠረቱ ነው! (የአሲምባ ርዕሰ አንቀጽ)

Assimba_Editorial_N04_05112014

Radio and Internet Access Still Denied in Ethiopia

Woyane has not stoped blocking

Video

ፍኖተ ህብረት፡ የኢሕአፓ ድምጽ ሬዲዮ